በመቀሌ የአሮጌው የብር ኖት በአዲስ መቀየር ማብቃቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

በመቀሌ የአሮጌው የብር ኖት በአዲስ መቀየር ማብቃቱን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– መቀሌን ጨምሮ ቅያሬው ከተጀመረ  14 ቀናት ባለፋቸው የትግራይ ከተሞች ሲሰጥ የነበረው የብር ቅያሬ አገልግሎት ከዛሬ ጀምሮ መቋረጡን ብሔራዊ ባንክ ገለጸ ፡፡

ዘግይተው ሥራ የሚጀምሩ ሌሎች የባንክ ቅርንጫፎች በከተማው አሮጌ ብር መቀየር የሚችሉት በተቀመጠላቸው ጊዜ ውስጥ ብቻ መሆኑም ተነግሯል፡፡
በዚህ መሠረት ከዛሬ ጥር 17 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በትግራይ አንዳንድ ከተሞች ቀድሞ አገልግሎት የሚጀምር የባንክ ቅርንጫፍ ሲኖር፤ የዚያ ከተማ የተራዘመ የብር ቅያሬ ጊዜ የሚቆጠረው ይኸው የባንክ ቅርንጫፍ በከተማው ቀድሞ ሥራ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ ለ14 ቀናት ብቻ እንደሚቆይ ብሔራዊ ባንክ ይፋ አድርጓል፡፡
እስካሁን የክልሉ የብር ቅያሬ አፈፃፀም ግምገማ መሰረት የተራዘመው ጊዜ ለእያንደንዱ የባንክ ቅርንጫፍ  የተሰጠ መሆኑ ቀርቶ ለእያንዳንዱ የክልል ከተማ እንዲሆን መደረጉንም ባንኩ ጠቁሟል።

LEAVE A REPLY