በአፋር ክልል የ71 ባለ ሀብቶች ፍቃድ ተሰረዘ

በአፋር ክልል የ71 ባለ ሀብቶች ፍቃድ ተሰረዘ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ የተሠማሩ የ71 ባለ ሀብቶችን ፍቃድ መሰረዙን የአፋር ክልል የኢንቨስትመንት ኮሚሽን ገለጸ።

ባለሀብቶቹ ከአራት አመት በፊት በሆቴልና ቱሪዝም ዘርፍ ለመሰማራት ፍቃድ ቢወስዱም እስካሁን ወደ ሥራ አለመግባታቸውን በኮሚሽኑ የኢንቨስትመንት ማበረታቻና መረጃ ዳይሬክተር አቶ እድሪስ እስማኤል ገልጸዋል።
ባለሀብቶቹ በክልሉ በቂልበቲ-ረሱ ዞን በአበአላ ከተማ አስተዳደር ለሆቴል ግንባታ የተረከቡት ከ67 ሺህ ካሬ ሜትር በላይ መሬት ወደ መሬት ባንክ ገቢ ተደርጓል።
በክልሉ ካለፉት ሁለት ዓመታት ወዲህ ካለው አስተማማኝ ሰላም በተጨማሪ በኢንቨስትመንት ዘርፍ ፍቃድ አሰጣጥን ጨምሮ ቀልጣፋ አገልግሎት እየተሰጠ በመሆኑ በዘርፉ የሚሠማሩ የሀገር ውስጥ እና የውጭ ባለ ሀብቶች ቁጥር እየጨመረ መጥቷል መባሉን ሰምተናል።

LEAVE A REPLY