ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮ ቴሌኮም ባለፉት ሥድሥት ወራት ያሉትን የደንበኞች ቁጥር 50 ነጥብ ሰባት ሚሊዮን ማድረሱን አስታወቀ።
የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ ይህ የደንበኞች ቁጥርም ካለፈው ተመሳሳይ አመት ጋር ሲነፃፀር የ 11 ነጥብ ሁለት በመቶ እድገት ማሳየቱን ገልጸዋል።
የአገልግሎት ዓይነቱ ተለያይቶ ሲታይ የሞባይል ድምፅ ደንበኞች ብዛት 48.9 ሚሊዮን ፣ የመደበኛ ብሮድባንድ ደንበኞች 309 ነጥብ አራት ሺሕ ፣ የመደበኛ ስልክ ደንበኞች 981 ሺሕ እንዲሁም የዳታ እና ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች 23 ነጥብ አምስት አራት ሚሊዮን እንደሆነ ከሥራ አስፈጻሚዋ ገለጻ መረዳት ተችሏል።