የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ እንዲወጡ የአሜሪካ መንግሥት አሳሰበ

የኤርትራ ወታደሮች በአስቸኳይ ከትግራይ እንዲወጡ የአሜሪካ መንግሥት አሳሰበ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ እየካሄደ ያለውነ ግጭት ተንተርሶ  ዝርፊያዎች፣ መደፈሮች፣ እንዲሁና በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ውስጥ ጥቃቶችና ሌሎች የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተለየዩ ወገኖች እየደረሱ መሆናቸውን ሪፖርቶች እንደደረሱት የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ቢሮ ገለጸ።

የተለያዩ ኃይሎች ጥሰቶቹን እየፈፀሙት ነው ያለውና በውጭ ጉደይ ቃል አቀባዮ በኩል ይፋ የሆነው የስቴት ዲፓርትመንት መግለጫ፤ አሜሪካ የኤርትራን ወታደሮች በተመለከተ ግልፅና የማያሻማ አቋም እንዳላት ጠቁሞ ወታደሮቹም ከክልሉ በአስቸኳይ እንዲወጡ ሲል አስጠንቅቋል።

በትግራይ የሚገኙት ወታደሮች ዝርፊያ፣ ወሲባዊ ጥቃት፣ በተጨማሪም በስደተኞች መጠለያ ካምፕ ላይ ጥቃትና ሌሎች ጥሰቶች እያደረሱ እንደሆነ ሪፖርቶች ደርሶኛል ያለችው አሜሪካ፤ በትግራይ ክልል የሚገኙ የኤርትራ ስደተኞችን የኤርትራ ወታደሮች አስገድደው ወደ ሀገራቸው እየመለሷቸው ነው ሲል ወቅሷል።

የኢትዮጵያ መንግስት ይህንን ክስ አስመልከቶ በተደጋጋሚ በሰጠው ምላሽ የሀሰት ፕሮፓጋንዳ ነው ሲል ሲያጣጥለው መሰንበቱ አይዘነጋም

LEAVE A REPLY