ሱዳን የያዘችውን መሬት እንደማትለቅ ድጋሚ አረጋገጠች

ሱዳን የያዘችውን መሬት እንደማትለቅ ድጋሚ አረጋገጠች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ሱዳን መልሳ የያዘችውንና በወረራ የተቆጣጠረችውን ከኢትዮጵያ የሚያዋስናትን ቦታ እንደማትለቅ አስታወቀች።

“ሱዳን ከአልፋሻጋ ይዞታ ቅንጣት ታህል እንደማትሰጥ ሜጀር ጀነራል ሀይደር አልቲራፊ አረጋግጠዋል። ለወታደራዊ ኃይል ምልመላ እየተደረገ መሆኑንም ተናግረዋል” ይላል ሲል የሱዳን መንግሥት ልሳን የሆነው ሱና መረጃውን ይፋ አድርጓል።

ኢትዮጵያ በበኩሏ አለመግባባቱን በድርድር ለመፍታት ሱዳን የያዘችውን መሬት እንድትለቅ እንደ ቅድመ ሁኔታ ብታስቀምጥም፤ የሱዳኑ ጀነራል  አልገዳሪፍ ውስጥ ፋላታ ከተባለው ጎሳ ድጋፍ በተቀበሉበት ወቅት ባደረጉት ንግግር “ሁሉም ዜጎች ልጆቻቸው ወታደራዊ ኃይሉን ተቀላቅለው የሀገራቸውን ዳር ድንበር እና ክብር እንዲያስጠብቁ እንዲያነሳሱ እጠይቃለሁ” ሲሉ ተደምጠዋል።

LEAVE A REPLY