ታመዋል የተባሉት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በይፋ ለሕዝብ ታዮ

ታመዋል የተባሉት ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በይፋ ለሕዝብ ታዮ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የሰሞኑን ሐሰተኛ ወሬ ተከትሎ የጤንነታቸው ጉዳይ አነጋጋሪ የነበረው ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ ዛሬ በቴሌቪዥን አማካይነት ለሕዝብ በይፋ ታይተዋል።

ጠቅላዮ በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል የሚገኘውን የሰው ሠራሽ አካል እና የአካል ድጋፍ ማደራጃ ድርጅትን ሲጎበኙ በርካታ የሀገር ውስጥ መገናኛ ብዙኃን አስመልክተዋል።

“ለተጎዱ የመከላከያ ሠራዊት አባላትና ለሲቪሎች የሚሠራውን ሰው ሠራሽ አካል ዛሬ ጎብኝቻለሁ። ከውጭ መጥተው በበጎ ፈቃደኝነት ይሄንን ታላቅ ሥራ የሚሠሩ ሰሎሞን አማረን የመሰሉ ወገኖች ሊበረታቱ ይገባል” ሲሉም ዶ/ር ዐቢይ በፌስ ቡክ እና በቲውተር ገጻቸው ሀሳባቸውን ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY