ኢትዮጵያ ለ64 ቀናት ኢንተርኔት በማቋረጧ 113 ሚሊዮን ዶላር አጣች

ኢትዮጵያ ለ64 ቀናት ኢንተርኔት በማቋረጧ 113 ሚሊዮን ዶላር አጣች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ኢትዮጵያ ካለፈው ዓመት መገባደጃ አንስቶ ለ1 ሺኅ 536 ሰዐታት ወይም 64 ቀናት የኢንተርኔት አገልግሎት ማቋረጧን ተከትሎ 111.3 ሚሊዮን ዶላር አጥታለች ተባለ።

የሀገራትን ኢንተርኔት ፍሰትን በሚከታተለው ኔት ብሎክስ በተሰኘው መንግሥታዊ ያልሆነ ድርጅት እና የኢንተርኔት መብትን በሚያቀነቅነው ዘ ኢንተርኔት ሶሳይቲ በተሰኙ ሁለት ኢንተርናሽናል ድርጅቶች ጥናት ነው ይህንን የክስረት አኃዝ ያረጋገጠው።

ኢትዮጵያ፤ የፖለቲካ ትኩሳት በጋለባቸውና አለመረጋጋቶች በተከሰተባቸው ወቅቶች ኢንተርኔት መዝጋቷን ጠቁሞ፤ በተለይም የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳን መገደል ተከትሎ በተቀሰቀሰ ሕዝባዊ ተቃውሞ የተነሳ፣ ከሰኔ እስከ ሐምሌ ባሉት ወራቶች ውስጥ፣ ከሦስት ሳምንት በላይ ኢንተርኔት ተቋርጦ እንደነበርም አስታውሷል።

 በትግራይ ክልል የህወሓት ኃይሎች ጥቅምት 4 ቀን 2013 ዓ.ም በክልሉ በሚገኘው የሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት መክፈታቸው ከተገለፀ በኋላ መንግሥት ሕግ የማስከበር ዘመቻ ያለውን እርምጃ ተከትሎ የስልክና የኢንተርኔት አገልግሎት ተቋርጦ መቆየቱም ያደረሰው የገቢ መቀነስ በዚህ ጥናት ውስጥ መካተቱን ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY