ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ታች አርማጭሆ ወረዳ በአንድ ግለሰብ አማካኝነት በህገ ወጥ መንገድ ወደ ባንክ ሊገባ የነበረ 29 ሺሕ ሐሰተኛ ባለ ሁለት መቶ የብር ኖት ተያዘ።

ሐሰተኛ የብር ኖቱ ትናንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ሳንጃ ቅርንጫፍ ሊገባ ሲል መያዙን የወረዳው ፖሊስ የወንጀል ምርመራ እፊሰር ዋና ሳጅን ማረልኝ ገልጸዋል።
ሐሰተኛ የብር ኖቶቹን ለማስገባት ሙከራ ያደረገው ግለሰብም በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለ ሲሆን፤
ፖሊስ ድርጊቱን በፈጸመው ግለሰብ ላይ ባደረገው ምርመራ ከወላጅ አባቱ ጋር በሬ ሸጠው ገንዘቡን እንደተቀበሉ ተናግሯል።

LEAVE A REPLY