በአዲስ አበባ ለተማሪዎች 400 ሺሕ ጥንድ ጫማ እየተመረተ ነው ተባለ

በአዲስ አበባ ለተማሪዎች 400 ሺሕ ጥንድ ጫማ እየተመረተ ነው ተባለ


ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የመንግሥት ትምህርት ቤት ለሚማሩ ተማሪዎች የሚቀርብ 400 ሺሕ ጥንድ ጫማ እየተመረተ ነው ተባለ፡፡

የከተማ አስተዳደሩ ለመንግሥት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ጫማ ለማቅረብ በያዘው እቅድ መሠረት በሀገር ቤት አምራች ኢንዱስትሪዎች 400 ሺህ ጫማ እንዲቀርብ ትዕዛዝ ተሰጥቶ እየተሠራ መሆኑን የገለጸው የኢትዮጵያ የቆዳ ኢንዱስትሪ ልማት ኢንስቲትዮት ነው፡፡
የኢንስቲዩቱ ዋና ዳይሬክተር አቶ ዳኛቸው ሽፈራው ይህን የተናገሩት የመሥሪያ ቤታቸውን የሥድሥት ወር የሥራ ክንውን ሪፖርት በሕዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት ለንግድና ኢንዱስትሪ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ባቀረቡበት ወቅት መሆኑንም ተመልክተናል።
በተመሳሳይ ለኦሮሚያ፣ ለአማራና ለሲዳማ ክልል ተማሪዎችም የሚሆን ጫማ ከቆዳ ኢንዱስትሪዎች ለማቅረብ የሙከራ ፕሮጀክት እንደተጀመረ ለማወቅ ተችሏል።

LEAVE A REPLY