ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት እነ ስብሐት ነጋ ለየካቲት 5 ተቀጠሩ

ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡት እነ ስብሐት ነጋ ለየካቲት 5 ተቀጠሩ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ስብሐት ነጋን ጨምሮ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔና ሌሎችም ከፍተኛ የቀድሞ የሕወሓት ሹማምንት ዛሬ ለሁለተኛ ጊዜ ፍርድ ቤት ቀረቡ፡፡

የፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት አራዳ ምድብ 1ኛ ጊዜ ቀጠሮ ችሎት የቀረቡት አቶ ስብሃት ነጋ፣ ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ፣ አምባሳደር አባዲ ዘሙ፣ ወ/ሮ ቅዱሳን ነጋ ፣ አቶ ቴዎድሮስ ሐጎስ፣ አቶ ወ/ጊዮርጊስ ደስታ እና ወ/ሮ ህሪቲ ምህረቱ መሆናቸው ታውቋል ፡፡
1ኛ ተጠርጣሪ አቶ ስብአት ነጋን ጨምሮ ተጠርጣሪዎች በአቶ ስዩም መስፍን የሚመራ ቡድን በመመስረት በሀገሪቱ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጠር ሲያስተባብሩ  እንደነበር  ማስረጃዎች  አሰባስቤያለሁ ያለው ፖሊስ፤ በተጨማሪም በሰሜን ዕዝ ላይ ጥቃት እንዲፈፀም ትግራይ የራሱ ዕዝ ሊኖረው ይገባል የሚል ሀሳብ በመያዝ ከተለያዩ ክልሎች ሰዎችን በመመልመል ብጥብጥ እንዲነሳ ትእዛዝ ሲሰጥ እንደነበር ማስረጃዎች ማግኘቱን ለፍርድ ቤት አስረድቷል፡፡
ዶ/ር ሰለሞን ኪዳኔ ህወሓት ለጦርነት የሚጠቀምበት ምሽግ እንዲቆፈር ሲያግዙ እንደነበር፣ መንግስት ለመጠባበቂያ ያስቀመጠውን ነዳጅ እንዲዘረፍ እና ለጦርነት ዓላማ እንዲውል በማድረግ ተጠርጥረዋል ያለው ፖሊስ፤ ለዚህም 15 የሰው ምስክሮች ቃል መቀበሉንም ገልጿል።
ተጠርጣሪዎች የተጠረጠሩበት ወንጀል ሰፊ እና ውስብስብ፤ ተጨማሪ ማስረጃዎችንም ማሰባሰብ  የሚጠይቅ ነው በማለት በመርማሪ ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ መጠየቁን ተከትሎ ለየካቲት 5 ቀን 2013 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።

LEAVE A REPLY