ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ ውስጥ በሚገኙ እንስሳት ላይ ከፍተኛ ህገ ወጥ አደን እየተካሄደ መሆኑን የፓርኩ ጽህፈት ቤት ገለጸ።
“በጋምቤላ ብሔራዊ ፓርክ የብዝሃ ህይወት ሀብት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ለመከላከል የባለድርሻ አካላት የተቀናጀ ትብብር ያስፈልጋል”ሲል የገለጸው የኢትዮጵያ ዱር እንስሳት ልማትና ጥበቃ ባለሥልጣን ነው።
በፓርኩ በሚገኙ የእንስሳት ሀብት ላይ ከፍተኛ ህገ ወጥ አደን እየተካሄደ መሆኑን የተናገሩት የፓርኩ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ ባለሙያ አቶ ሄኖከ ታምሩ፤ በተለይም የነጭ ጆሮ ቆርኪ እና ዝሆኖች ላይ ከፍተኛ አደን እየተካሄደ መፈጸሙን ጠቁመው፤
በዘንድሮ ብቻ አምስት ዝሆኖችም ተገድለዋል ብለዋል።
የቀድሞ የፓርኩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ የአሁኑ የጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ ምክትል ፕሬዚዳንት ዶክተር ጋልዋክ ኮርት ቀደም ሲል በፓርኩ ከ550 በላይ ዝሆኖችና ከ1 ሚሊዮን የሚበልጡ የነጭ ጆሮ ቆርኪዎች እንደነበሩ አስታውሰዋል።