ባልደራስ፣ አብን እና መኢአድ ጥምረት ለመፍጠር ከስምምነት ደረሱ

ባልደራስ፣ አብን እና መኢአድ ጥምረት ለመፍጠር ከስምምነት ደረሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቀጣዮ ምርጫ ላይ ተወዳዳሪ ከሆኑት ድርጅቶች መካከል ባልደራስ ለእውነተኛ ዲሞክራሲ፣ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና መኢአድ (መላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት) ጥምረት ሊፈጥሩ ነው ተባለ።

ሦስቱ ፓርቲዎች ከአንድ አመት በፊት በተመሳሳይ ጥምረት ለመፍጠር ድርድር ጀምረው የነበረ ቢሆንም አብን በስተመጨረሻ ራሱን በማግለሉ በእስክንድር ነጋ የሚመራው አብን እና የማሙሸት አማረ መኢአድ ለመቀናጀት መቻላቸው ይታወሳል።
አሁን ላይ ሦስቱ ፓርቲዎች በጋራ ጥምረት ምርጫውን ለመወዳደር ከቅድመ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የኢትዮጵያ ነገ የአዲስ አበባ ዘጋቢ የባልደራስ እና የአብን ከፍተኛ አመራሮችን አነጋግሮ ማረጋገጥ ችሏል።
ፓርቲዎቹ በተለይም ከቅርብ ጊዜ በበሳል ምሁራን የተዋቀረው ኢዜማ ከፍተኛ የሕዝብ ድጋፍ ያገኛል ተብሎ በተገመተበት አዲስ አበባ ላይ ትኩረት እንዳደረጉ እና ጥምረቱም እንዳስፈለጋቸው ውስጥ አዋቂዎች በመናገር ላይ ናቸው።

LEAVE A REPLY