ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ባህር ዳር ከተማ በህገ ወጥ መንገድ የተከማቸ 11 በርሜል ነዳጅ በቁጥጥር ሥር መዋሉን የባህር ዳር ፖሊስ አስታወቀ፡፡
ጥር 25/2013 ዓ.ም ከሕዝብ በደረሰ ጥቆማ በባሕር ዳር ከተማ በአንድ ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ 11 በርሜል ነዳጅ እንዲሁም ለጥቁር ገበያ የተዘጋጀ 20 ባለሁለት ሊትር የውኃ ማሸጊያ ሀይላንድ ቤንዚን በቁጥጥር ስር ማዋሉን በባሕር ዳር ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ6ኛ ዋና ፖሊስ ጣቢያ የማኅበረሰብ አቀፍ ወንጀል መከላከል ዘርፍ ኃላፊ ምክትል ኢንስፔክተር ንብረት ተፈራ ተናግረዋል፡፡
የተያዘው ነዳጅ የዘርፉ ፈቃድ በሌለው ግለሰብ መኖሪያ ቤት ውስጥ ነው ያሉት ምክትል ኢንስፔክተሩ ፤ ንብረቱ ለጥቁር ገበያው መበራከት አንድ ምክንያት የሆነውን እጥረት መፍታት ይገባል ሲሉም ተደምጠዋል።