ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በሀገሪቱ በሚታዮ አንዳንድ እንቀስቃሴዎች ሳቢያ በትግራይ ቀጣዮን ምርጫ ለማካሄድ አመቺ ሁኔታ እንደሌለ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ አስታወቀ።
ምርጫ ቦርድ እስካሁን ባለው እቅዱ በፀጥታ ችግር ምክንያት የትግራይ ክልልን አለማካተቱን ያስታወሱት የቦርዱ የኮምዩኒኬሽን ዳይሬክተር ሶልያና ሽመልስ፤
የማንነት ጥያቄ ያለባቸው አካባቢዎችም ተመሳሳይ ዕጣ እንደገጠማቸው ጠቁመዋል።
የማንነት ጥያቄ በቀረበባቸው ቦታዎች ምርጫ አይካሄድባቸውም ወይ? ለሚለው ጥያቄ፤
ቦርዱ ምንም እንኳን የፀጥታ ጉዳይ ተቋማዊ ዐቢይ ተግባሩ ባይሆንም ፤ የወሰንና ማንነት ጉዳዮች በሚመለከታቸው አካላት ውሳኔ ሲያገኙና ምርጫ ለማካሄድ አመቺ ሁኔታዎች ካሉ ቦርዱ ምርጫ ማካሄድ ይችላል ብለዋል።