ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በአዲስ አበባ ከተማ መዋቅራዊ ዕቅድ ላይ የተቀመጡት 15 ተርሚናሎች/ጣቢያዎች ሲሆኑ በዕቅዱ መሰረት ሥራ ላይ የዋሉት አምስት ብቻ መሆናቸው ደግሞ ከተማ አስተዳደሩ በአፈጻጸም ረገድ ችግር ያለበት መሆኑን አሳይቷል።
የተሰሩት ተርሚናሎች/ጣቢያዎች መገናኛ፣ ሳርቤት፣ አየርጤና፣ ዊንጌት እና ቦሌ የሚገኙ መሆናቸውን የጠቆመው ዜና፤ ቀሪዎቹ የሲኤምሲ፣ የቦሌ ለሚ፣ የኮተቤ፣ የቤላ/ፈረንሳይ፣ የአቅም ግንባታ/ከስድስት ኪሎ በስተሰሜን፣ የፒያሳ፣ የቃሊቲ እና የቆጣሪ ተርሚናሎች እንዳልተገነቡ ይፋ አድርጓል።