በሥድሥተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዓለም ዐቀፍ ታዛቢዎች ይገኛሉ ተባለ

በሥድሥተኛው ሀገራዊ ምርጫ ዓለም ዐቀፍ ታዛቢዎች ይገኛሉ ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በግንቦት ወር መጨረሻ እና ሰኔ መጀመሪያ ላይ በሚካሄደው ሀገራዊ ምርጫ ላይ በርካታ ዓለም ዐቀፍ እና ሀገር በቀል ታዛቢዎች ይገኛሉ ተባለ።

ለንደን የሚገኘው ቻትሃም የተሰኘው ገለልተኛ የዓለም አቀፍ ጉዳዮች ተቋም በመጪው የኢትዮጵያ ምርጫ ዙሪያ ባዘጋጀው የበይነ መረብ ውይይት ላይ ከላይ የሰፈረውን ሀሳብ የተነሠገሩት የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ት ብርቱኳን ሚዴቅሳ፤ ምርጫውን ከሌላው ጊዜ የተሻለ ለማድረግ እንደሚሠሩ ገልጸዋል።
በውይይቱ ላይ የቦርዱ ከወ/ት ብርቱኳን በተጨማሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዶ/ር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ ፣ የኢትዮጵያ ማሕበራዊ ዴሞክራሲ ፓርቲ ሊቀ መንበር ፕ/ር በየነ ጴጥሮስ እና የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ፤ ኢዜማ ሊቀመንበር ፕ/ር ብርሃኑ ነጋ መሳተፋቸው ታውቋል።
በመጪው ምርጫ ላይ በተሳታፊነት ለመሳተፍ ከ170 በላይ የሲቪክ ማሕበራት ማመልከቻ ማስገባታቸውን የቦርዱ ሰብሳቢ በውይይቱ ላይ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY