ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የወደብ አገልግሎትን ያቀላጥፋሉ በሚል የተገዙ 49 የወደብ ማሽኖች ወደ ሀገር ቤት ገብተው ርክክክብ መካሄዱ ተሰማ።
የማሪታይም ጉዳይ ባለስልጣን የሚመራው ሎጅስቲክስ ማዕከል የሞጆ ሎጅስቲክስ ማዕከል ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ ከሀምሌ 2009 ዓ.ም ጀምሮ በመተግበር ላይ ሲሆን፤ የፕሮጀክቱ አካል የሆነው እና የሞጆ ደረቅ ወደብ አቅምን ለመገንባት፣ ብሎም ለማዘምን የሚያስችሉ 49 የወደብ ማሽኖች ግዢ ተፈፅሞ ዛሬ የርክክብ ሥነ ሥርዓቱ ተካሂዷል።
ማሽኖቹ ከዓለም ባንክ በተገኘ 19 ነጥብ 6 ሚሊየን ዶላር ብድር ግዢው የተፈፀመ ሲሆን የፕሮጀክቱን 13 በመቶ እንደሚሸፍኑ በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የትራንስፖርት ሚንስትሯ ዳግማዊት ሞገስ ገልጸዋል።