ዛሬ እነ ጃዋር መሐመድ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ጋዜጠኞች ችሎቱን እንዳይታደሙ ተከለከሉ

ዛሬ እነ ጃዋር መሐመድ ፍርድ ቤት ሲቀርቡ ጋዜጠኞች ችሎቱን እንዳይታደሙ ተከለከሉ

A high-profile Ethiopian activist, Jawar Mohammed is photographed during an interview, in Addis Ababa on October 25, 2019. - A high-profile Ethiopian activist at the centre of violence that left 16 people dead this week has accused Prime Minister Abiy Ahmed of acting like a dictator and said he might challenge him in elections planned for next year. (Photo by Michael Tewelde / AFP) (Photo by MICHAEL TEWELDE/AFP via Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና–  “በረሃብ አድማው ደክመዋል” የተባሉት ጃዋር መሐመድ፣ በቀለ ገርባ እና ሐምዛ አዳነ ፍርድ ዛሬ ቢቀርቡም፣ የችሎቱን ሂደት ጋዜጠኞች እና የሰብኣዊ መብት ድርጅት ባልደረቦች እንዳይታደሙ ተከልክለዋል።

ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ ሲናፈሱ የነበሩትን ወሬዎች ተከትሎ ዛሬ ቀጠሮ የነበራቸው እነ ጃዋር መሐመድ በችሎቱ ይገኛሉ ተብሎ አልተጠበቀም። በተለይም የተጠርጣሪዎቹ ጠበቆች ቢቢሲ እና ኦ ኤም ኤን ላይ “እነ ጃዋር ደክመዋል፣ ተነስተው ሊያነጋግሩን ባለመቻላቸው የታሠሩበት ክፍል ድረስ ለመግባት ተገደናል፣ የጤንነታቸውም ሁኔታ ያሳስበናል ” በማለት ትናንት መናገራቸው ግምቱን ይበልጥ አጠናክሮታል።
ይሁን እንጂ ደክመዋል የተባሉት ፖለቲከኞች ዛሬ በቀጠሮአቸው መሠረት ከችሎት ላይ መገኘታቸው እንዴት ሊሆን ቻለ? የሚል ጥያቄን በቅዙዎች ዘንድ የፈጠረ ሲሆን፤ ምናልባትም ጋዜጠኞቹ እና የሰብኣዊ መብት ድርጅት ባልደረቦቹ እንዳይገቡ የተከለከለው አስቀድሞ በሐሰት የተናፈሰውን ወሬ እንዳያጋልጡ ሊሆን ይችላል ተብሏል።
በፀረ ሽብርና ሕገ-መንግሥታዊ አንደኛ ችሎት ዛሬ ማለዳ በእነ አቶ ጃዋር መሐመድ የክስ መዝገብ የተከሰሱ የ24 ተከሳሾች የእምነት ክህደት ቃል ለመቀበል ቀጠሮ ተይዞ የነበረ ቢሆንም አስፈላጊውን ቅደም ተከተል አሟልተው ወደ ችሎቱ የገቡ ጋዜጠኞች እና የሰብኣዊ መብት ተቋማት ባልደረቦች በፀጥታ ኃይሎች ተለይተው እንዲወጡ መደረጋቸውን አረጋግጠናል።
 የፌደራል ፖሊስ እና የአዲስ አበባ ፖሊስ አባላት የቢቢሲን ሪፖርተር ጨምሮ 8 ጋዜጠኞችን እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ባልደረባ ከችሎቱ በማስወጣት የፍርድ ሂደቱን እንዳይከታተሉ የገደቡ ሲሆን ያደረጉትም ከበላይ በተሰጠ ትዕዛዝ እንደሆነ አስረድተዋል።

LEAVE A REPLY