ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን እንዲያጣራ የተቋቋመው ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ

ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን እንዲያጣራ የተቋቋመው ግብረ ኃይል መቀሌ ገባ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ተፈጸመ የተባለውን የጾታ ጥቃት የሚያጠራ ግብረ ኃይል መቋቋሙ ተነገረ።

ከጤና ሚንስቴር፣ ከሴቶች፣ ህጻናት እና ወጣቶች ሚንስቴር፣ ከአገር መከላከያ እና ከጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተወጣጡ አባላትን ያካተተው ግብረ ኃይል መቀሌ ከተማ በመግባት የምርመራ ሥራውን ጀምሯል።
ከፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ኃይሎች መካከል የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ተደጋጋሚ ጾታን መሰረት ያደረጉ ጥቃቶች እየደረሱ ስለመሆኑ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትን ጨምሮ በርካታ ዓለም ዐቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች መግለጻቸው ይታወሳል።

LEAVE A REPLY