ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ከምርጫ ጋር በተያያዘ የሚነሱ ችግሮች ላይ ብቻ የሚሰራ አዲስ የምርጫ ምርመራ ዴስክ አቋቁሚያለሁ አለ።
ፖሊስ ገለልተኛ በሆነ መልኩ መጪው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲከናወን ሓላፊነቱን ለመወጣት ዝግጁ መሆኑንም ጠቁሟል።
የፌደራል ፖሊስ ምክትል ኮሚሽነር ጀኔራል ዘላለም መንግስቴ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተዘጋጀው አዲስ ወግ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ፖሊስ በምርጫው ላይ ያለውን ዝግጁነት በሚመለከት መልእክት ባስተላለፉበት ነው ይህን የተናገሩት።