ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ የኮቪድ – 19 ጫናን በመቋቋም በቱሪዝሙ ዘርፍ የሰራችውን ስራ በመገምገም የጉዞ ደህንነት ማረጋገጫ እውቅና ከአለም ጉዞና ጉብኝት ም/ቤት ማግኘቷ ተሰማ።
የኢትዮጵያን የቱሪዝም ኢንዱስትሪ መልሶ ለማነቃቃት ደህንነቱ የተጠበቀ የጉብኝት እንቅስቃሴ ማረጋገጥ የሚያስችሉ ፕሮቶኮሎች ተዘጋጅተው ተግባራዊ መሆናቸውን የባህል እና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ሂሩቴ ካሳው ተናግረዋል።
ሀገራት የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በመከላከል ደህንነቱ የተጠበቀ የጉብኝት እንቅስቃሴ እያደረጉ ሲሆን ኢትዮጵያም ከኮቪድ ጋር በመሆን የሰራችው ሥራ በዓለም ጉዞና ጉብኝት ም/ቤት መገምገሙ ተሰምቷል።