ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የህወሓት ጁንታ በትግራይ ክልል በተለያዮ ከተሞች በሚገኙ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ ባደረሰው ጥፋት ከ240 ሚሊዮን ብር በላይ ጉዳት ማድረሱ ተረጋገጠ።
ይህን ያህል ከባድ ኪሳራ ሀገር እና እወክለዋለለሁ በሚለው ሕዝብ ላይ ከሃዲው ቡድን ቢያደርስም፤ ለ116 ኪሎ ሜትር የኤሌክትሪክ መስመር ፈጣን ጥገና ተደርጎ በከፍተኛ ወጪ መጀመሩን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ድርጅቱ አስታውቋል።
በትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ መሠረተ ልማት ላይ ጁንታው ባደረሰው ጥፋት ከ240 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት ጉዳት ደርሷል ያሉት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል የኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን፤ በዚህም ከክልሉ ባሻገር ከባህርዳር አላማጣ፤ ከኮምቦልቻ አላማጣ እንዲሁም ከተከዜ አክሱም፣ ከአሸጎዳ መቀሌ በሁለት አቅጣጫዎች የሚገኙ የኃይል ማስተላለፊያ መስመሮች ለከፋ ጉዳት ተዳርገዋል ብለዋል።