ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ክልል ተጨማሪ ከተሞች የስልክ አገልግሎት መጀመሩን ኢትዮ ቴሌኮም አስታወቀ።
በክልሉ የተከሰተውን ግጭት ተከትሎ ተቋርጦ የነበረው የስልክ አገልግሎት በ363 ጣቢያዎች እንደተጀመረም ተነግሯል።
ድርጅቱ በሰሜን ሪጅን የቴሌኮም መሰረተ ልማት ጥገና እና አገልግሎትን በተመለከተ በሰጠው መግለጫ እስካሁን ድረስ የጥገናና የኃይል አቅርቦት ስራዎች በመጀመር በ363 ጣቢያዎች የሞባይል ድምፅና የመደበኛ ስልክ አገልግሎት ተጀምሯል ብሏል።
መቀለ፣ አድዋ፣ አክሱም፣ አዲግራት፣ ሽረ እንዳስላሴ፣ ነጋሽ፣ ዲንሻ፣ ውቅሮ፣ አዳጋ ሃሙስን ጨምሮ ሀያ ስድስት ከተሞች የኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎት ተጠቃሚ እንደሆኑም ታውቋል።
መከላከያ ሠራዊት መቀለን ከተቆጣጠረ ጥቂት ሳምንታት በኋላ በደቡብና ምዕራብ ትግራይ የሚገኙት አንዳንድ ከተሞች ተቋርጦ የቆየውን አግልግሎት መጀመሩ አይዘነጋም።