ኢትዮጵያ ከአዲሱየአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እንደምትሠራ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

ኢትዮጵያ ከአዲሱየአፍሪካ ሕብረት ሊቀ መንበር እንደምትሠራ ዶክተር ዐቢይ አሕመድ ገለጹ

Ethiopia's Prime Minister Abiy Ahmed (C) arrives at Khartoum international airport on June 7, 2019. - Ethiopia's prime minister arrived in Khartoum today seeking to broker talks between the ruling generals and protesters as heavily armed paramilitaries remained deployed in some squares of the Sudanese capital after a deadly crackdown, leaving residents in 'terror'. (Photo by ASHRAF SHAZLY / AFP) (Photo credit should read ASHRAF SHAZLY/AFP/Getty Images)

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ኢትዮጵያ ከአዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ፌሌክስ ሺሴኬዲ ጋር በትብብር እንደምትሠራ ገለጹ።

አዲሱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀ መንበር ሆነው ለተመረጡት የዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ፕሬዚዳንት ፌሌክስ ሺሴኬዲ የእንኳን ደስ አለወት መልክዕት ያስተላለፉት ዶክተር ዐቢይ አሕመድ፤ ኢትዮጵያ ለተመራጩ ሊቀ መንበር ድጋፍ ታደርጋለች፣ አብራም ትሠራለች ብለዋል።
በአዲስ አበባ ይካሄዳል በተባለው የአፍሪካ ሀገራት ጉባዔ ላይ የሚሳተፉ የተለያዮ ሀገራት ዲፕሎማቶች እና ባለሥልጣናት ዛሬ ወደ ኢትዮጵያ መግባት መጀመራቸውን ተከትሎ አዲስ አበባ ከረፋድ እስከ ምሽት ድረስ በከፍተኛ የትራፊክ መጨናነቅ ተወጥራ ውላለች።

LEAVE A REPLY