ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የዓለም ምግብ ድርጅት እና የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ ለሚያሻቸው ሰዎች ድጋፍ ለማድረስ ከስምምነት እንደደረሱ ተነገረ።
በተባባሩት መንግሥታት የዓለም ምግብ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዴቪድ ቢዝሊይ የኢትዮጵያ መንግሥት እና ድርጅታቸው በመላው ትግራይ የሰብዓዊ ድጋፍ ለማድረስ ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን አረጋግጠዋል።
“በትግራይ ሦስት ሚሊዮን ሕዝብ የእኛን አስቸኳይ እርዳታ ይሻል። የምናባክነው ጊዜ የለም” ያሉት ዳይሬክተሩ፤
የዓለም ምግብ ድርጅት 1.3 ሚሊዮን ሕዝብ ለመርዳት 20 ሺህ ቶን ምግብ በመላው ትግራይ እያሰራጨ መሆኑን በተንቀሳቃሽ ምስል አማካይነት ለዓለም አጋርተዋል።