ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፍልሰተኞች ፖሊሲ ለመጀመሪያ ጊዜ እያዘጋጀሁ ነው አለ

ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የፍልሰተኞች ፖሊሲ ለመጀመሪያ ጊዜ እያዘጋጀሁ ነው አለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የፍልሰተኞች ፖሊሲ እየተዘጋጀ እንደሆነ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ አስታወቀ።

ኢፌዴሬ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ከፍተኛ የሕግ ባለሙያ የሆኑት አቤል ገብረእግዚአብሄር ፤ ከዚህ በፊት በሠራተኞች፣ እንዲሁም በዲያስፖራዎች ዙሪያ የወጡ እንጂ በፍልሰት ዙሪያ የተጠቃለለ እና ሁሉንም ያማከለ ፖሊሲ አልነበረንም ሲሉ ተናግረዋል።
 ከ 2011 መጨረሻ ጀምሮ ግን አቅጣጫ በማስቀመጥ በጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሪነት ከሠራተኛ እና ማህበራዊ ጉዳይ፣ ማዕከላዊ ስታትስቲክስ፣ ፕላን እና ልማት ኮሚሽን እንዲሁም ከሌሎች ተቋማት ጋር በመሆን ኮሚቴ በማዋቀር  ፖሊሲውን ለማዘጋጀት ጥረት ተደርጓል ነው የተባለው።
ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ የመጣውን ፍልሰተኝነትን ለመከላከል የሚያስችለው ፖሊሲ ሲረቀቅ ዓለም ዐቀፍ አማካሪ ተደርጎ በትኩረት እየተሠራበት ነው ተብሏል።

LEAVE A REPLY