ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቀጣዩ ሀገር አቀፍ ምርጫ ላይ መረጃ በመስጠትና ሁነቶችን በመዘገብ ለሚሳተፉ ጋዜጠኞች በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ በ450 ሺህ ዶላር ወይንም ከ17 ሚሊየን ብር በላይ በሆነ ወጪ የአቅም ግንባታ መስጠት ጀመረ።
ጋዜጠኞች ለመራጮች የተለያዩ ሃሳቦችን በማቅረብ እንዴት ማስተማር እንደሚችሉ፣ ተአማኒና ግልጽ መረጃን በማድረስ ደግሞ ሃላፊነታቸውን እንዴት መወጣት እንደሚችሉ ክህሎት ማስጨበት የሚያስችሉ ስልጠናዎች ያገኛሉ ተብሏል።
ስልጠናው በጆን ሆፕኪንስ ዩኒቨርሲቲ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ እና ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እንዲሁም በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የጆርናሊዝምና ኮሙኒኬሽን ትምህርት ክፍል በጋራ የተዘጋጀ ነው።
ለሀያ አምስት ሳምንታት በሚዘልቀው ስልጠና ከ500 እሰከ 700 ለሚሆኑ ጋዜጠኞች ተሳታፊ ይሆናሉ።