ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ለሥድሥተኛው ሀገር ዐቀፍ ምርጫ ለእጩዎች ምዝገባ የሚያገለግሉ ሰነዶችና ቁሳቁሶች ዛሬ መሰራጨት እንደሚጀምሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ይፋ አደረገ።
ቦርዱ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ከፍተኛ አመራሮች ጋር በሀገራዊው ምርጫ ዙሪያ እየመከረ ሲሆን፤
ለምርጫ እጩዎች፣ ለመራጮች እና ለድምጽ አሰጣጥ የሚያገለግሉ ሰነዶችና ቁሳቁሶች ዝግጅት መጠናቀቁ በውይይቱ ላይ ተገልጿል።
ሰነዶቹ እና ቁሳቁሶቹ የሚሰራጩት በሦስት ምዕራፍ ተከፋፍሎ መሆኑን ያስታወቀው ቦርዱ፤ ለዕጩዎች ምዝገባ የሚያገለግሉ ሰነዶችና ቁሳቁሶች ከዛሬ ጀምሮ መሰራጨት እንደሚጀምሩም አረጋግጧል።
ለመራጮች ምዝገባ እና ለድምጽ አሰጣጥ የሚያገለግሉ ሰነዶችና ቁሳቁሶችም በቀጣይ እንደሚሰራጩም ከወዲሁ ተገልጿል።