ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር የአዲሱን ብር ለውጥ ተከትሎ የወጣው የብሄራዊ ባንክ መመሪያ አላሠራንም አሉ።
መንግሥት በድንገተኝነት ይፋ ያደረገውን የብር ለውጥ ተከትሎ ያወጣቸው የተለያዮ የአጠቃቀም መመሪያዎች ከግለሰብ ጀምሮ እስከ ትልልቅ ተቋማት ከፍተኛ ቅሬታ ሲያሰነዝሩ ቆይቷል።
ሰሞኑን የኢትዮጵያ ኮንስትራክሽን ሥራ ተቋራጮች ማኅበር የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ ያወጣው ህግ በ24 ሰዐት ውስጥ ማውጣት የሚቻለው የከፍተኛ የገንዘብ መጠን ጣሪያው 75 ሺኅ ብር መሆኑ እና እንዲሁም በሳምንት አምስት ትራንዛክሽን ብቻ ነው መፈፀም የሚቻለው የሚለው መመሪያ ሥራቸውን በእጅጉ እንዳስተጓጎለባቸው ገልጸዋል።
የኮንስትራክሽኑ ዘርፍ በቢሊዮን የሚቆጠር ከፒታል የሚያንቀሳቅስ መሆኑ እየታወቀ በቀን ሠባ አምስት ሺኅ ብር ብቻ እንድናወጣ አልተፈቀደልንም ያሉት የማኅበሩ አባላት፤ በዚህ ወቅት ለኮንስትራክሽን ሥራ የሚያሴፈልጉ እቃዎች ዋጋ በሚሊዮን የሚቆጠር መሆኑ ለሥራችን እንቅፋት ሆኗል ብለዋል።