በትግራይ 108 የመደፈር ጥቃቶች መድረሳቸውን ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ

በትግራይ 108 የመደፈር ጥቃቶች መድረሳቸውን ሰብአዊ መብት ኮሚሽን ገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ 108 የመደፈር ጥቃቶች ለጤና ተቋማት ሪፓርት መደረጋቸውን የኢትዮጵያ ሰብኣዊ መብት ኮሚሽን አስታወቀ።

ኮሚሽኑ በመቀለ ከሚገኙ የህክምና ባለሙያዎች እንዲሁም ከጊዜያዊ አስተዳደሩ ጤና ቢሮ ባገኘው መረጃ መሠረት፤ ባለፉት ሁለት ወራት ብቻ በመቀለ ሆስፒታል 52፣ በአይደር ሆስፒታል 27፣ በአዲግራት ሆስፒታል 22፣ በውቅሮ ሆስፒታል 7 በአጠቃላይ 108 የመደፈር ጥቃቶች ለጤና ተቋማት ሪፖርት መደረጋቸውን በዛሬ መግለጫው ጠቁሟል።
በክልሉ የተጣለው የሰዐት እላፊ ገደብ የሕክምና እርዳታ ፈላጊዎች በምሽት ወደ ጤና ተቋማት እንዳይሄዱ እንቅፋት እንደሆነም የገለጸው ኢሰመኮ፤በጦርነቱ ሳቢያ የአዕምሮ መረበሽ የገጠማቸው ሕጻናትን እንዳገኘም ገልጿል።

LEAVE A REPLY