በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲደረግ ክራይሲስ ግሩፕ ጠየቀ

በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲደረግ ክራይሲስ ግሩፕ ጠየቀ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በትግራይ ክልል የኢትዮጵያ የውጭ አጋሮች የመብት መርማሪዎችና ሚዲያዎች ያለ ምንም እክል በመላው ትግራይ እንዲንቀሳቀሱ በኢትዮጵያ መንግሥት ላይ ጫና እንዲያደርጉ ክራይሲስ ግሩፕ ጠየቀ።

“Finding a Path to Peace in Ethiopia’s Tigray Region” በሚል ርዕስ ባወጣው የ19 ገፅ ሪፖርት ይፋ ያደረገው ክራይስስ ግሩፕ  ሀገሪቷ ወደ ሰላም በዘላቂነት የምትመለስበትን፣ ከትግራይ ክልል ጋር ያለው ግጭት በቋሚነት የሚፈታበት መንገድ ያለውን ተጨማሪ ነጥቦችን ያካተተ ነው ተብሏል።
ቡድኑ ለአሜሪካ መንግሥት፣ ለአውሮፓ ሕብረትና ለአፍሪካ ሕብረት እንዲሁም ሌሎች አጋሮች የመብት ተመራማሪዎች እና ሚዲያዎች ያለምንም እክል ገብተው ሥራቸውን እንዲያከናውኑ የኢትዮጵያ ባለስልጣናት እንዲፈቅዱ ጫና እንዲያደርጉ ጥያቄ አቅርቦ፤ ተፈፀሙ የሚባሉ ጥሰቶች በሙሉ በገለልተኛ አካል እንዲጣራ እነዚሁ አካላት ጫና ሊያደርጉ እንዲያደርጉ ተገልጿል።

LEAVE A REPLY