ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በትግራይ ክልል የሚገኙ ከ12 ሺህ በላይ የሚሆኑ የ12ኛ ክፍል አገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ፈተናውን በዩኒቨርስቲዎች ይወስዳሉ ተባለ።
በአካባቢው የትምህርት መሠረተ ልማቶች ሙሉ ለሙሉ በመውደማቸው ፈተናውን በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስትሩ ዶክተር ጌታሁን መኩሪያ ገልጸዋል።
ተፈታኞች በቀጣዮቹ ጥቂት ሳምንታት በክልሉ ወደሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት እንደሚጓጓዙ የተናገሩት ሚኒስትሩ፤ ፈተናቸውን የሚወሰዱባቸው ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት መቀለ፣ አክሱም፣ አዲግራት እና ራያ የኒቨርስቲዎች እንደሆኑም አብራርተዋል።
በኦንላይን ይሰጣል ተብሎ የነበረው የ12ኛ ክፍል ፈተና ከየካቲት 29፣ 2013 ዓ. ም ጀምሮ በወረቀት እንደሚሰጥ የትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል።