በቤኒሻንጉል 120 ሽፍቶች እጃቸውን ለመንግሥት ሰጡ

በቤኒሻንጉል 120 ሽፍቶች እጃቸውን ለመንግሥት ሰጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በቤኒሻንጉል ጉሚዝ ክልል መተከል ዞን ማንዱራ ወረዳ 120 ሽፍቶች በዞኑ ለተቋቋመው የተቀናጀ ግብረ ኃይል በሰላማዊ መንገድ እጃቸውን መስጠታቸው ተነገረ።

የምዕራብ ዕዝ ህብረት ዘመቻ ኃላፊ ተወካይ ኮ/ል ፋሲል ይግዛው፣  ሽፍቶቹ በህወሓት  ቡድን የሀሰት ትርክት ጫካ ገብተው እንደነበረ ጠቁመው፤ በጫካ የነበሩ የሽፍታው ቡድን አባላት በሠላማዊ መንገድ እንዲገቡ፣ የሀገር ሽማግሌዎች፣ የመከላከያ መረጃ ዋና መምሪያ እንዲሁም ብሔራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት በጋራ ጉልህ አሴተዋጽኦ ማበርከታቸው ተነግሯል።
በጫካ ሽፍቶችን ሲመራ የነበረው ላቀው ደረጄ እና አዲሱ ፈጠነ የተባሉት ሽፍቶች፤ የህወሓት ቡድኑ መቐሌ በመጥራት ሲያሰለጥናቸው እንደነበረ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY