ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በዩኔስኮ በርካታ ቅርሶችን ያስመዘገቡ ዐሥር የዓለም ሀገራት ዝርዝር ውስጥ ኢትዮጵያ ሳትካተት ቀረች።
የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ድርጅት (ዩኔስኮ) ትኩረት ያሻቸዋል፤ ድንቅ ናቸውና እንክብካቤ ይደረግላቸው፣ ይጠበቁ ደግሞም ጎብኚዎችም ይጎብኗቸው ሲል ቅርሶችን ሲመዘግብ መቆየቱ ይታወቃል።
ይህን ተከትሎ የዓለም ሀገራት በተፈጥሮ የታደሉትንም ሆነ በባህል የተቸሩትን ቅርስ ሲያስመዘግቡ በቆዮት መሠረት በርካታ ቅርስ ያስመዘገቡ ዐሥር ሀገሮች ሰሞኑን ይፋ ተደርገዋል።
በዚህ መሠረት ጣልያን እና ቻይና እያንዳንዳቸው ሀምሳ አምስት ቅርሶችን በማስመዝገብ የአንድኝነቱን ደረጃ ይዘዋል። አሥራ ሦስት ያህል ቅርሶችን ያስመዘገበችው ኢትዮጵያ ከቀዳሚ ዐሥሩ የዓለም ሀገራት ዝርዝር ውስጥ መካተት አልቻለችም።