ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– አስተማማኝ የሆነ ሰላም የራቃት መቀለ ከተማ አሁንም ቢሆን ሙሉ በሙሉ ወደ መደበኛ እንቅስቃሴዋ መመለስ አልቻለችም ተባለ።
የተወሰነ በሚባል ወይም ደግሞ ምንም አይነት የሰዎች እንቅስቃሴ የለም የሚሉት የትግራይ ነዋሪዎች፤ “ሱቆችም ሆኑ የግል ተቋማት ተዘግተዋል። በከተማዋ ውስጥ የትራንስፖርት አገልግሎት የለም” ሲሉ ለቢቢሲ ገልጸዋል።
ሰሞኑን በመቀለ ከተማ ከተነሳው ረብሻ ጋር ተያይዞ በሽረ፣ አዲግራት እንዲሁም ከመቀለ 45 ኪሎሜትር ርቀት ላይ በምትገኘው ውቅሮ ከተሞችም በርካታ የህወሓት ደጋፊ የሆኑ ግለሰቦች ለተቃውሞ አደባባይ መውጣታቸውን ተከትሎ ስምንት ሰዎች መገደላቸው ተሰምቷል።
ተቃውሞው ተገቢ አይደለም ያሉት የመቀለ ከተማ የህዝብ ግንኙነት ሓላፊ አቶ ጠዓመ፤ “ለዘረፋ ለስርቆት እንዲመቻቸው ተራ ዱርየዎች ያወጁት ተቃውሞ ነው” ሲሉም ረብሻውን ገልጸውታል።