ኢትዮጵያ በየአመቱ 1 ሺሕ 500 አዞዎችን ብታርድም ስጋና ቆዳውን ለገበያ የማቅረቡ ሂደት...

ኢትዮጵያ በየአመቱ 1 ሺሕ 500 አዞዎችን ብታርድም ስጋና ቆዳውን ለገበያ የማቅረቡ ሂደት አዝጋሚ ነው ተባለ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዞ ምርቶችን በገበያ ትስስር ችግር ምክንያት በሚፈለገው ደረጃ ለገበያ ማቅረብ አለመቻሉን የአርባ ምንጭ አዞ እርባታ ጣቢያ ገለጸ።

በደቡብ ክልል አርባ ምንጭ ከተማ የሚገኘው የአርባ ምንጭ አዞ እርባታ ጣቢያ በ1976 ዓ.ም የተመሰረተና  የአዞ እርድ በማከናወን ቆዳና ስጋ ወደ ውጭ ሲልክ ቢቆይም በታሰበለት ልክ ፍሬያማ ሊሆን አልቻለም።
 ከ1983 እስከ 1992 ዓ.ም ድረስ 11 ሺህ ቆዳ ለዓለም ገበያ ቀርቧል ያሉት የጣቢያው ጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ወንደሙ አባተ ፤ ከ1992 ዓ.ም ጀምሮ ምርቱ ለዓለም ገበያ ያልቀረበው የገበያ ትስስር በሚፈለገው ደረጃ ባለመኖሩ መሆኑንም አስረድተዋል።
በ2010 ዓ.ም ለምርት የደረሱ 1ሺሕ 500 አዞዎች የገበያ ትስስር ባለመፈጠሩ ታርደው ቆዳቸው እንዲቀመጥ የተደረገ ሲሆን፤ በየዓመቱ እስከ ሁለት ሺሕ የአዞ ቆዳ ለዓለም ገበያ ለማቅረብ እቅድ ቢያዝም በተለያዩ ችግሮች ሳቢያ እቅዱን ማከናወን አልተቻለም ተብሏል።
አንድ ሳንቲ ሜትር የአዞ ቆዳ እስከ አምስት ዶላር፣ አንድ ኪሎግራም ስጋ ደግሞ 20 ዶላር ድረስ የሚሸጥ ቢሆንም ለጉዳዩ ትኩረት ባለመሰጠቱ ሀገሪቱ ከዚህ የምታገኘውን ገቢ እንድታጣ ተደርጓል።

LEAVE A REPLY