የአዳነች አቤቤ አስተዳደር ለ”ከነራ” ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ የ46 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ሰጠ

የአዳነች አቤቤ አስተዳደር ለ”ከነራ” ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ የ46 ሚሊዮን ብር ፕሮጀክት ሰጠ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የወሳኝ ኩነት መረጃ እና ምዝገባ ኤጀንሲ የራሱ የመረጃ ማከማቻ ቋት (ዳታ ሴንተር) ባለቤት ሊሆን ነው ተባለ።

የመረጃ ቋት ግንባታው እየተጠናቀቀ እንደሆነ እወቁልኝ ያለው ኤጀንሲው፤ ለዚህም ከ49 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ መደረጉን ይፋ አድርጓል።
“ከነራ” ኢንተርናሽናል ትሬዲንግ ዛሬ የመረጃ ማከማቻ ቋትን ሥራ ለማስጀመር ጥናት አድርጎ ያጠናቀቀበትን ሰነድ እና የሚተከለው እጅግ ዘመናዊ የዳታ ቤዝ መሳሪያ ዝርዝር ሂደቱን ማጠናቀቁ ተሰምቷል።
የኤጀንሲው ዋና ዳየሬክተር ዶ/ር ታከለ ነጫ ኤጀንሲው የራሱ የሆነ የመረጃ ማከማቻ ቋት እና የሰነድ ማከማቻ ባለቤት መሆኑ እስካሁን የነበረውን የኔት ወርክ መቆራረጥ ከማስቀረቱም በላይ መረጃዎችን በሶፍት እና በሀርድ ኮፒ ለመያዝ ያስችላል ብለዋል።
ዲጂታል አገልግሎት ለመስጠት፣ ቀልጣፋ አገልግሎት ለመስጠት እና የህዝብ እርካታ ለማምጣት እንደሚያስችላቸው የጠቆሙት ሓላፊው፤  ከነራ የተሰኘው ድርጅት ፕሮጀክቱን ቀ49ሚሊዬን 600,000 ጨረታውን እንዳሸነፈ ገልጸዋል።

LEAVE A REPLY