ኢዜማ በሽሮ ሜዳ አካባቢ ቅስቀሳ እንዳያደርግ ፌደራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ...

ኢዜማ በሽሮ ሜዳ አካባቢ ቅስቀሳ እንዳያደርግ ፌደራል ፖሊስ እና አዲስ አበባ ፖሊስ አባላት አገዱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና || ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ያወጣውን የጊዜ ሰሌዳ ተከትሎ ፓርቲዎች ቅስቀሳ ማካሄድ ጀመሩ።

ቦርዱ ፓርቲዎች ከዛሬ ከየካቲት 8 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ እስከ ግንቦት 23 ቀን 2013 ዓ/ም የምረጡኝ የቅስቀሳ ዘመቻ ማድረግ እንደሚችሉ መግለጹ አይዘነጋም። ዛሬ ምርጫ በሚደረግባቸው የወረዳ መዋቅሮቹ የምረጡኝ ቅስቀሳ የጀመረው የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ከወዲሁ እንቅፋት ገጥሞታል።
በአዲስ አበባ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች የተሳተፉበት የቅስቀሳ ዘመቻ የትራንስፖርት አገልግሎት በመስጠት ጭምር የተከናወነ ቢሆንም፤ በተለምዶ ሽሮሜዳ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ለማድረግ አቅዶት የነበረው ዘመቻ በፌደራል እና አዲስ አበባ ፖሊስ አባላት እንዲታገድ ተደርጓል።
ኢዜማን እንዳይቀሰቅስ የከለከሉት የተደራጁ የሁለቱ ፖሊስ ኮሚሽን አባላት “ምርጫ ቅስቀሳ ስለመጀመሩ አናውቅም” የሚል ምላሽ መሰጠታቸው ደግሞ በብዙዎች ዘንድ ግርምትን ፈጥሯል።

LEAVE A REPLY