በመላው የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገለጸ

በመላው የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡ ተገለጸ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– ዳግም በመላው የትግራይ ክልል የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መቋረጡን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለጸ።

በክልሉ የኃይል መቋረጥ ያጋጠመው ከትናንት ማክሰኞ የካቲት 10/2013 ዓ. ም ከሰዓት በኋላ ጀምሮ መሆኑን የጠቆመው ተቋሙ፤ መንግሥት “የጁንታው ርዝራዦች” ያላቸው ታጣቂዎች በክልሉ ባለ የኤሌክትሪክ መሰረተ ልማት ላይ በፈፀሙት ጥቃት በመላው ትግራይ የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት ለመቋረጥ መገደዱን አረጋግጧል።
ይህ በእንዲህ እንዳለ የጁንታው አባላት በተበታተነ መንገድ ወደ ሕብረተሰቡ በመግባት በመሠረተ ልማቶች ላይ ጥቃት እየፈጸሙ ናቸው ያለው የትግራይ ክልል ጊዚያዊ አስተዳደር፤ ሕዝብ የጁንታው አባላትን እንዳያስጠጋ አሳርቧል።
ሕብረተሰቡ ይህን የማያደርግ ከሆነ እና ወንጀለኞችን በጉያው የሚያቅፍ ከሆነ በሚደርሰው ጥቆማ መሠረት እርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ ገልጿል።

LEAVE A REPLY