በአምስት አመታት ውስጥ 5 ሺሕ የሦስተኛ ዲግሪ ምሩቃንን የሚያፈራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

በአምስት አመታት ውስጥ 5 ሺሕ የሦስተኛ ዲግሪ ምሩቃንን የሚያፈራ ፕሮጀክት ይፋ ሆነ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በአምስት ዓመታት 5 ሺሕ የሶስተኛ ዲግሪ ምሩቃንን ለማፍራት የሚያስችል ፕሮጀክት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አደረገ።

በትብብርና ትስስር ተግባራዊ የሚሆነው “Home Grown Collaborative PhD Programs” በሁሉም መስክ ብቁ የሆኑ መምህራንን በማቅረብ የትምህርት ጥራትና አግባብነት ለማስጠበቅ በሚደረገው ጥረት ውስጥ ወሳኝ ድርሻው የጎላ ነው ተብሎለታል።
ለሀገር የታሰበውን የልማትና ብልጽግና ጉዞ ለማሳከት ብቃት ያላቸው መምህራን፣ ሳይንቲስቶችና ተመራማሪዎችን ማፍራት ወሳኝ ነዉ ያሉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕሮፌሰር አፈወርቅ ካሱ፤ በበኩላቸው ሀገሪቱ ያላትን ሃብትና አቅም በማስተባበር፣ ብሎም በሚገባ በመጠቀም እውቀትና ክህሎት ያለው ዜጋ ለማፍራት በሚደረገው ጥረት ውስጥ የከፍተኛ ትምህርትና ስልጠና ተቋማት የሀገር ውሰጥና ዓለም ዐቀፍ ትብብር ከትስስሮች ጋር በማጠናከር ለፕሮግራሙ መሳካት የድርሻቸውን እንዲወጡ መልእክት አስተላልፈዋል።

LEAVE A REPLY