ጦር ኃይሎች ሆስፒታል የተወሰዱት በቀለ ገርባ “አልታከምም” ብለው ተመለሱ

ጦር ኃይሎች ሆስፒታል የተወሰዱት በቀለ ገርባ “አልታከምም” ብለው ተመለሱ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና– በረሃብ አድማ ላይ ናቸው የሚባሉት አቶ በቀለ ገርባ ያለ ፍላጎታቸው በአስገዳጅ ሁኔታ ወደ መንግሥታዊው የጤና ማዕከል ጦር ሃይሎች ሆስፒታል ተወስደዋል ሲሉ ጠበቆቻቸው ቅሬታቸውን አሰሙ።

ከፍርድ ቤት ትዕዛዝ ውጪ የህግ አግባብ በተጣሰበት ሁኔታ አቶ በቀለ በተወሰዱበት ጦር ኃይሎች ሆስፒታል አልታከምም ማለታቸውም ተነግሯል።
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የፀረ ሽብር እና በሕገ-መንግስት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ችሎት ሰኞ እለት የካቲት 8፣ 2013 ዓ.ም እነ አቶ በቀለ ገርባን በግል የጤና ተቋም በሆነውና ቂርቆስ ክፍለ ከተማ በሚገኘው ላንድ ማርክ ሆስፒታል እንዲታከሙ ውሳኔ ቢያስተላልፍም፤ ከረሃብ አድማው ጋር በተያያዘ ለሕመም የተዳረጉት በቀለ ገርባ ወደ ጦር ኃይሎች ሆስፒታል እንዲወሰዱ ተደርጓል።
አቶ በቀለ ገርባ ከጥር 19፣ 2013 ዓ.ም ጀምሮ ከውሃ ውጪ ምንም ምግብ ሳይመገቡ ቆይተዋል የሚሉት ጠበቆቻቸው፤ የፍርድ ቤቱ ውሳኔ ተሽሮ ወደ መንግሥት የሕክምና ተቋም እንደሚወሰዱ ሲነገራቸው ግለሰቡ ወደ ቃሊቲ መልሱኝ ቢሉም ሰሚ አላገኙም ሲሉም ተደምጠዋል።
ጦር ኃይሎች ሆስፒታል ከደረሱ በኋላም ለአራት ሰዐታት ያህል ሕክምና እንዲያደርጉ አቶ በቀለ ገርባ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው ወደ ማረሚያ ቤት እንዲመለሱ ተደርጓል።

LEAVE A REPLY