ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተፈናቅለው በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ለሚገኙ ዜጎች 6 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉን በኢትዮጵያ የስዊዲን ኤምባሲ ገለጸ።
በኢትዮጵያ የስዊዲን አምባሳደር ሃንስ ሄነሪክ ሉንድኩዊስት የተመራ ልዑክ በቻግኒ ከተማ የሚገኙ የመተከል ዞን ተፈናቃዮችን የጎበኘ ከመሆኑ ባሻገር፤ ከአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳደር አቶ አገኘው ተሻገር እና ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር ተወያይተዋል።
የስዊድን መንግሥት ለተፈናቃይ ዜጎች በዩኒሴፍ በኩል 6 ሚሊዮን ዶላር የሚያወጣ የሰብአዊ ድጋፍ ያደረገ ቢሆንም በቀጣይ ተጨማሪ እርዳታዎችን ለመስጠት ማሰቡን ገልጸዋል።