ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በቤኒሻንጉል ጉምዝ መተከል ዞን የሚኖሩ ብሔር ብሔረሰቦችን ስብጥር መሰረት ያደረገ የአመራር ሽግሽግ እየተደረገ ነው ተባለ።
በዞኑ ጸጥታን እያስከበረ የሚገኘው የተቀናጀ ግብረ ኃይል አባላት በዳንጉር፣ ማንዱራ፣ ወምበራ፣ ቡለንና ድባጤ ወረዳዎች የተደረገውን የአመራር ሽግሽግ ተመልክቶ ለአመራሮቹ የሥራ መመሪያ መስጠቱንም ጀነራል አስራት ዲሮ ገልጸዋል።
ከዚህ በፊት የነበረው የአመራር ስብጥር በአመዛኙ በዞኑ የሚኖሩትን ብሔር/ብሔረሰቦች ታሳቢ ያላደረ ነበር ያሉት ጀነራሉ፤ ይህም በዞኑ የጸጥታ ችግር እንዲባባስና የተወሰነ አካል ተጎጂ እንዲሆን አስተዋፅዖ አድርጓል ሲሉ አስረድተዋል።