ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ኢትዮጵያ ዜጎች ለማሕበራዊ ፍትሕ /ኢዜማ/ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብሩን በግዮን ሆቴል እያካሔደ ይገኛል።
‘ንቁ ዜጋ፣ ምቹ አገር’ በሚል መሪ ሀሳብ እየተካሄደ ባለው የማስተዋወቂያ መርሃ-ግብር የፓርቲው ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች፣ ተወዳዳሪ ዕጩዎችና ደጋፊዎች መታደማቸውን ተመልክተናል።
የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ የሺዋስ አሰፋ መርሀ-ግብሩን ሲከፍቱ እንዳሉት ፓርቲው በ2013 ምርጫ በሰው ኃይል አደረጃጀት፣ በፖሊሲና በሌሎችም በቂ ዝግጀት ማድረጉን ጠቁመው፤ ፓርቲው ቢመረጥ አገሪቱን ማስተዳደር እንደሚችል ለማሳየት ዛሬ በይፋ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርሃ-ግብር እያካሄደ ይገኛል ሲሉ ተሰምተዋል።