የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል መንግሥታት ለሲዳማ ምሥረታ 130 ሚሊዮን ብር ሰጡ

የኦሮሚያ እና የአማራ ክልል መንግሥታት ለሲዳማ ምሥረታ 130 ሚሊዮን ብር ሰጡ

ኢትዮጵያ ነገ ዜና በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ባለው የሲዳማ ክልል የምስረታ ክብረ በዓል ላይ የክልል መንግሥታት የገንዘብ ድጋፍ እያደረጉ ነው።

በዚህ ክብረ በዓል ላይ በሽመልስ አብዲሳ የሚመራው የኦሮሚያ ክልል 100 ሚሊዮን ብር፣ የአማራ ክልል የ30 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸው ተሰምቷል።
የሶማሌ ክልል 10 ሚሊዮን፣ የሐረሪ ክልል 5 ሚሊዮን፣ የአፋር ክልል 7 ሚሊዮን ፣ እንዲሁም የጋምቤላ ክልል የ2 ሚሊዮን ብር፣ የአርሲ ዞን 1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ያደረጉ ሲሆን፤  የሻሸመኔ ከተማ አስተዳደር በበኩሉ የ1 ነጥብ 5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል ተብሏል።
በተያያዘ  ዜና በጨቅላው የሲዳማ ክልል ምሥረታ ክብረ በዓል የተገኙት የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በከተማ አስተዳደሩ ስም የ50 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል።

LEAVE A REPLY