ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– በፌዴራል መንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተያዙ ክፍት ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ በግል ባለሀብቶች እንዲለሙ ሊደረግ የሚያስችል አሠራር ተዘርግቷል ተባለ።
በአዲስ አበባ በሚገኙ የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች በተያዙ ቦታዎች ውስጥ ያሉ ክፍት ቦታዎች ላይ የተለያዩ የልማት ሥራዎችን ለመሥራት የመሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ፍቃደኛ ለሆኑ ፣ ብሎም የቢዝነስ ሀሳብ ካላቸው ሰዎች ጋር በጋራ ለማልማት እቅድ አለኝ ሲል እቅዱን ይፋ አድርጓል።
የአዲስ አበባ ከተማ ካለት 54 ሺሕ ካሬ የቆዳ ስፋት ውስጥ 5 ነጥብ 48 የሚሆነው በፌደራል የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች የተያዘ እንደሆነ የመሬት ባንክ እና ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሌንሳ መኮንን ጠቁመዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ወደ ሥልጣን መምጣትን ተከትሎ በአዲስ አበባ ውስጥ በልማት ስም በርካታ መሬቶች ለአመታት በባለ ሀብትች ተይዘው መቅየታቸውን ተከትሎ ወደ መሬት ባንክ እንዲገቡ መደረጋቸው ይታወሳል።