ኢትዮጵያን ጨምሮ የ10 ሀገራት ዜጎች ኦማን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

ኢትዮጵያን ጨምሮ የ10 ሀገራት ዜጎች ኦማን ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ አገደች

ኢትዮጵያ ነገ ዜና ኦማን ኢትዮጵያን ጨምሮ የ10 ሀገራት ዜጎች ለሁለት ሳምንታት ወደ ሀገሯ እንዳይገቡ እገዳ ጣለች።

ሀገሪቱ ይህን እርምጃ የወሰደችው እየተስፋፋ የመጣውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል እንደሆነ ጠቁማ፤ ይህ እገዳ ከመጪው ሀሙስ ጀምሮ ለተከታታይ አስራ አምስት ቀናት ተግባራዊ እንደሚሆንም አረጋግጣለች።
ወደ ሀገሯ እገዳ ከጣለችባቸው ሀገራት ዜጎች መካከል 8ቱ ከአፍሪካ ሲሆኑ፤ እነርሱም ከደቡብ አፍሪካ፣ ሱዳን፣ ናይጄሪያ ፣ ታንዛኒያ ፣ጋና ፣ኢትዮጵያ ፣ ጊኒ እና ሴራሊዮን መሆናቸው ታውቋል።
ከተጠቀሱት በተጨማሪ  የተጣለው የሊባኖስ እና ብራዚል መንገደኞች ወደ ኦማን እንዳይገቡ የታገዱ ሲሆን፤ እገዳው ከውጭ ወደ ሀገር የሚገቡ የኦማን ዜጋ የሆኑ ዲፕሎማቶች፤ የጤና ሠራተኞች እና ቤተሰቦቻቸውን እንደማያካትት ተገልጿል።

LEAVE A REPLY