ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ደቡብ ሱዳን ውስጥ የነበሩ አስራ አምስት የኢትዮጵያ ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ከደቡብ ሱዳን ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አንፈልግም አሉ።
ደቡብ ሱዳን ውስጥ በሰላም ማስከበር ላይ ተሰማርተው የነበሩ 169 ወታደሮችን በሌሎች ለመተካት በትናትናው ዕለት ወደ አዲስ አበባ ይመለሱ የነበሩ ቢሆንም፤ የትግራይ ተወላጅ የሆኑ 15 የሰላም አስከባሪው ኃይል አባላት ወደ ኢትዮጵያ መመለስ አንፈልግም ብለዋል።
ሱዳን ፖስት የተሰኘው ጋዜጣ በበኩሉ ወታደሮቹ ወደ ኢትዮጵያ መመለስ የማይፈልጉት በትግራይ ክልል መንግሥት እያካሄደ ካለው የሕግ ማስከበር እርምጃ ጋር በተያያዘ የሚደርስባቸውን ባለማወቃቸው ፍርኃት የገባቸው በመሆኑ ነው ሲል ሱዳን ፖስት ጋዜጣ ዘግቧል።
ገዳዩን አስመልከተው መግለጫ የሰጡት ሜጀር ጄኔራል መሐመድ ተሰማ ድርጊቱን የፈፀሙት በተባበሩት መንግሥታት ወሰጥ የሚሰሩ እና በአካባቢው የመኖሩ የጁንታው ደጋፊዎች በሚያደረጉት ውዥንብር የታለሉ ወታደሮች መሆናቸውን ገለፀዋል።
ወደ ኢትዮጵያ አንመለስም ያሉት ወታደሮች በአሁኑ ሰዐት በደቡብ ሱዳን ብሔራዊ የደኅንነት አገልግሎት ጥበቃ ስር እንደሚገኙ ታውቋል።