ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– ሠባት ሺህ የሚጠጉ ዜጎች ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን በአንድ ወር ውስጥ ተሰደው ወደ ሱዳን መግባታቸው ታወቀ።
ባለፈው አንድ ወር ውስጥ ብቻ በሺዎች የሚቆጠሩ ሰዎች ከምዕራባዊው የኢትዮጵያ ከፍል የመተከል ዞን ተፈናቅለው ወደ ጎረቤት ሱዳን መሸሻቸውን አሁንም እንደቀጠሉ የተባበሩት መንግሥታት የስደተኞች ኮሚሽን ገልጿል።
ከኢትዮጵያ ወጥተው ወደ ሱዳኗ የብሉ ናይል ግዛት የገቡት ሰዎች ቁጥር 7 ሺህ ይደርሳል ያሉት የኤጀንሲው ቃል አቀባይ ብባር ባሌክ፤ እስካሁን 3 ሺህ የሚሆኑትን መመዝገብ መቻሉንም አስረድተዋል።