ኢትዮጵያ ነገ ዜና፡– የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት ከዋናው የኤሌክትሪክ መረብ (ግሪድ) በመስመር ዝርጋታ የማያዋጣ የኤሌክትሪክ አገልግሎት ቦታዎች ላይ በአማራጭ የኃይል አቅርቦት ለደንበኞቹ ለማቅረብ መሰናዶውን አጠናቀቀ።
የኤሌክትሪክ ኃይል ለሕብረተሰቡ በሁለት መንገድ እንደሚደርስ እና ከዋናው መስመር በጣም የራቁ፣ እንዲሁም በመስመር ኃይል ለማቅረብ እጅግ ከፍተኛ ወጭ ለሚጠይቁ 25 የገጠር ከተሞች ከፀሐይ ኃይል በሚገኝ የኤሌክትሪክ ኃይል መብራት በስድስት ወራት ውስጥ እንዲያገኙ የሚያስችል ስምምነት ተቋሙ መፈራረሙ ተሰምቷል።
የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል አገልግሎት የኮርፖሬት ኮሙኒዩኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር መላኩ ታዬ ይህ አማራጭ ለሕብረተሰቡም ሆነ ለተቋሙ ጥቅሙ የጎላ ነው ብለዋል።